የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት በአማርኛ ቋንቋ
|
ትምህርት አንድ
መጽሐፍ ቅዱስ ማለት ምን ማለት ነው/ የቃሉ አመጣጥ ከወዴትና ምንስ ያመለክታል? መጽሐፍ ቅዱስ ቃሉ እንደሚያመለክተው መጽሐፍ እና ቅዱስ የሚሉ የሁለት ቃላት ጥምረት ነው፡፡ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ ወረቀት ወይም በብራና ከተጻፈ በኋላ በሁለት በትሮች የሚጠቀለል መጽሐፍ ያመለክታል፡፡ ቢብሎስ በእንግሊዝኛው ባይብል ተብሎ ሲተረጎም በአማርኛው ደግሞ መጽሐፍ በሚለው ቃል ተተረጎመ፡፡ የግሪኩ ቃል ቢብሎስ (byblos) እራሱ ቢብሎሰ (byblos) ከተባለ ከተማ ስም የተገኘ ነው፤ እርሱም ከኒቂያ ወደቦች መካከል በቤይሩት 25 ማይል ያህል የሚገኝ አገር ነው፡፡ለመጽሐፍ ያገለግል ዘንድ ፓፒረስ (ደንገል) የተባለውን ተክል እንደ ወረቀት አድርገው ይሠሩበት የነበረ ቦታ ነው፡፡ ቀጣዪን ከዚህ ያንብቡ... |
Recent PostsTopicsመጽሐፍ ቅዱስ ምን ማለት ነው Archives
March 2021
|
![]()
|